ማህደረ መለኮት

ማህደረ መለኮት(2x)
ማርያም እመ ብዙሀን(2x)
መለኮት ያደረብሽ ከፍጥረት ተለይተሽ
ከሁሉ የተወደድሽ ንፅህት ክብርት ነሽ
ከቃል በላይ ቃል አለኝ ለክብርሽ መገለጫ
ገናንነትሽ በአለምም ድንግል ሆይ አለው ብልጫ
ማርያም እመ ብዙሀን(2x)
አላወዳድርሽም በምንም በማንም
ወልደሽ ስለሰጠሽኝ ፍቅርና ሰላም
ማርያም ማርያም እልሻለሁ ደግሜ ደጋግሜ
በወለድሽው መድሀኒት ስለቀለለ ሸክሜ
ማርያም እመ ብዙሀን(2x)
ተወስኗል በሆድሽ ያልቻሉት ሰማያቱ
በማህፀንሽ ሆኖ ያስገርማል መታየቱ
ሰባ ሰገል ተደንቀው ቤተልሔም ተገኙ
ወርቅ እጣንና ከርቤ ሊገብሩ ለአዳኙ
ማርያም እመ ብዙሀን(2x)
አላወዳድርሽም በምንም በማንም
ወልደሽ ስለሰጠሽኝ ፍቅርና ሰላም
ማርያም ማርያም እልሻለሁ ደግሜ ደጋግሜ
በወለድሽው መድሀኒት ስለቀለለ ሸክሜ
ማህደረ መለኮት(2x)
ማርያም እመ ብዙሀን(2x)

††† ††† †††
 

Download it here

ማህደረ መለኮት

ማህደረ መለኮት(2x)
ማርያም እመ ብዙሀን(2x)
መለኮት ያደረብሽ ከፍጥረት ተለይተሽ
ከሁሉ የተወደድሽ ንፅህት ክብርት ነሽ
ከቃል በላይ ቃል አለኝ ለክብርሽ መገለጫ
ገናንነትሽ በአለምም ድንግል ሆይ አለው ብልጫ
ማርያም እመ ብዙሀን(2x)
አላወዳድርሽም በምንም በማንም
ወልደሽ ስለሰጠሽኝ ፍቅርና ሰላም
ማርያም ማርያም እልሻለሁ ደግሜ ደጋግሜ
በወለድሽው መድሀኒት ስለቀለለ ሸክሜ
ማርያም እመ ብዙሀን(2x)
ተወስኗል በሆድሽ ያልቻሉት ሰማያቱ
በማህፀንሽ ሆኖ ያስገርማል መታየቱ
ሰባ ሰገል ተደንቀው ቤተልሔም ተገኙ
ወርቅ እጣንና ከርቤ ሊገብሩ ለአዳኙ
ማርያም እመ ብዙሀን(2x)
አላወዳድርሽም በምንም በማንም
ወልደሽ ስለሰጠሽኝ ፍቅርና ሰላም
ማርያም ማርያም እልሻለሁ ደግሜ ደጋግሜ
በወለድሽው መድሀኒት ስለቀለለ ሸክሜ
ማህደረ መለኮት(2x)
ማርያም እመ ብዙሀን(2x)

††† ††† †††
 

Download it here

ማርያም ድንግል

ማርያም ድንግል ንጽህት
ምልእተ ጸጋ ደስ ይበልሽ
እመቤቴ /2x/ ፊትሽ ወድቄ ልሳለምሽ /2x/
የቆምሽበትን አከብራለሁ
በስእልሽ ፊት እሰግዳለሁ
ነፍሴ እንድትነፃ ከበደል
ዘወትር ከፊትሽ እማልዳለሁ
ግዞተኛ ነኝ በአለም
ነፃነቴ ነሽ ማርያም
አዝ . . . . . . . . .
የአሴቦን ልጆች ከእሩቅ
የጢሮስ ልጆች ከምስራቅ
መጡ ገስግሰው በደስታ
እናትነት ሽን ለማድነቅ
አምሐ ይዤ ለክብርሽ
እኔም ቆሜያለሁ ከደጅሽ
አዝ . . . . . . . . .
አጋንንት ፈሩ በሞገሷ
ልታማልደን ስትነሳ
እፁብ ነው ፍቅሯ በረከቷ
የአለምን ፍቅር የሚያስረሳ
ስምሽ ሲጠራ ለትውልድ
ዘወትር ይኖራል ሲያማልድ
አዝ . . . . . . . . . /2x/

††† ††† †††
 

Download it here

ምስጋና ነው ስራዬ

ምስጋና ነው ስራዬ
በዘመኔ በእድሜዬ
ለዋለልኝ ውለታ
ምን ልክፈለው ለጌታ
ትናንትና ጥልቁ ነበረ መኖሪያዬ
የማዳኑ ቀኑ ደረሰ የጌታዬ
ራቁቴን ሸፍኖልኛል በብርሃኑ
ምግቤ ሆኗል ስሙን ማወደስ በየቀኑ
አዝ . . . . . . . . . . . .
አልተራብኩም አልተጠማሁም በዘመኔ
ምግበ ስጋ ምግበ ነፍስ ነው ጌታ ለእኔ
ተበጥሷል የእሳቱ ገመድ ሰንሰለት
አልረሳውም የርሱን ውለታ ብድራት
አዝ . . . . . . . . . . . .
ማን ያፈቅራል አስከ ሞት ድረስ ዋጋ ከፍሎ
ማን ያድናል ባለስልጣኑን ሞትን ገድሎ
አማኑኤል በፍቅሩ ጸዳል ምድርን ከድኖ
ሰው አርጎኛል የማይሆኑትን ሁሉ ሆኖ
አዝ . . . . . . . . . . . .
እንዴት ሆኜ ፍቅሩን ልግለጸው እንዴት ብዬ
ስለ እጆቹ በእምባ ጨቀየ መኝታዬ
በእርሱ ቁስል ነፍሴ ወጥታለች ከመከራ
በዝማሬ ስሙን ማክበር ነው የኔ ሰራ
አዝ . . . . . . . . . . . . /2x/

††† ††† †††
 

Download it here

ምስጋናዬን ለአምላኬ አቀርባለሁ

ምስጋናዬን ለአምላኬ አቀርባለሁ
በማደሪያው ገብቼ እሰግድለታለሁ
ኤልሻዳይ ነው ጌታ ሁሉን ቻይ
ይፈጸማል አምናለሁ የልቤ ጉዳይ
ዘንባባዬን ይዤ እንደ ህጻናቱ
ሆሳእና ልበለው ሰግጄ በፊቱ
ምንም ባዶ ብሆን እውቀት ቢጎድለኝ
ለስሙ ልዘምር ከልካይም የለኝ

አዝ . . . . . . . . . . . .
አምላኬ በፊት ህ ቃል አለብኝ እኔ
ቋንቋዬ መዝሙር ነው ያንተ እንደመሆኔ
በአሚናዳብ ደጃፍ በቅድመ ታቦቱ
ያ የክብርህ ኡደት ጠራኝ ማህሌቱ

አዝ . . . . . . . . . . . .
የህይወት ትርጉሜ አንተ ነህ ደስታዬ
ስምህን ማገልገል ክብሬ ነው ስራዬ
ለታመነው ጌታ ምስክር የሆኑ
ከብረው ተመለሱ ለበረከት ሆኑ

አዝ . . . . . . . . . . . .
መነሻዬ አንተ ነህ ጉልበቴና ክብሬ
መድረሻዬም አንተ መደምደሚያ ቅጥሬ
በጽዮን ተራራ ስትገለጽ ያኔ
ነጩን ልብስ አልብሰህ አስነሳኝ ለቅኔ

አዝ . . . . . . . . . . . . /2x/

††† ††† ††† ††† †††
 

Download it here

ሰላሜ በአንተ ነው


ሰላሜ በአንተ ነው የኔ ጌታ
እረፍቴ በአንተ ነው የኔ ጌታ
አልከለከል ምስጋና አልከለከል ውዳሴ ለአንተ ውለታ
ጨለማዬ በአንተ በራልኝ
ከሰው ትከሻ ወረድኩኝ
የምመራበት ዱላዬ
በአንተ ተጥሏል ጌታዬ
አሁን በግላጭ አያለሁ
ሙሉ ሰው በአንተ ሆኛለሁ

አዝ . . . . . . . . . . . .
የመውገርያው ድንጋይ ቀረልኝ
ጠላቴ በፊቴ አፈረልኝ
በፊትህ አቆምከኝ በጸጋ
ገዝተኸኛልና በዋጋ
ለውለታህማ ምን እላለሁ
ተመስገን ብዬ አልፈዋለሁ

አዝ . . . . . . . . . . . .
ሰላላው እጄን አቅንተሃል
ሽባነቴንም ተርትረሃል
ደካማነቴ ተወገደ
ያ ክፉ መንፈስ ተሰደደ
ታውጆልኛል ነጻነቴ
አመልክሃለሁ በህይወቴ

አዝ . . . . . . . . . . . .
የአይኔ ላይ ቅርፊት ወለቀ
ሸክሙ ከላዬ አለቀ
በደማስቆ ብርሃን መታኸኝ
የራስህ ምርጥ እቃ አደረግከኝ
ያ ሁሉ ድካሜ አለፈ
ልቤ ለፍቅርህ ተሸነፈ

አዝ . . . . . . . . . . . . /2x/
††† ††† †††
 

Download it here

በዙፋኑ ፊት በላይ ያለው

በዙፋኑ ፊት በላይ ያለው
የጌታ መልአክ ከኔ ጋር ነው
ከኔ ጋር ነው አልፈራም ሞገዱን
ከእኔ ጋር ነው ጠባቂዬ እርሱ ነው
ከእኔ ጋር ነው አልፈራም እሳቱን
ከእኔ ጋር ነው ታምኜ እወጣለሁ
ምህረት ይለምናል ፍቅርና ይቅርታ
ከታመነው ንጉሥ ከሠራዊት ጌታ
አጽንቷል እግሮቹን እንዳይናወጹ
ባህሩን አቁሟል የሚካኤል ድምጹ
አዝ . . . . . . . . . . . .

ወርዷል ከሰማያት ክንድን ሊያበረታ
ሚካኤል ወዳጄ የነፍሴ እፎይታ
ይዘረጋል ክንፉን ረበበ በላዬ
ያጅበኛል ሁሌ ከፊት ከኋላዬ
አዝ . . . . . . . . . . . .

የነሐሱ መውጊያ ደጆቹን ቆረጠ
ከእስረኞቹ መሃል ልጁን አስመለጠ
አደገድጋለሁ ለዚህ ባለክብሩ
የፅዮን ካሕናት በደስታ ዘመሩ
አዝ . . . . . . . . . . . .

ምህረት ይለምናል ፍቅርና ይቅርታ
ከታመነው ንጉሥ ከሠራዊት ጌታ
አጽንቷል እግሮቹን እንዳይናወጹ
ባህሩን አቁሟል የሚካኤል ድምጹ
አዝ . . . . . . . . . . . . /2x/
 

Download it here

ባለ ጸጋ እመቤት

ባለ ጸጋ እመቤት ባለ ጸጋ እመቤት ባለ ጸጋ እናት
አፍሰናል ከደጅሽ ብዙ በረከት
ወጀቡን ቀዝፈናል ብለን ማርያም
እንዘምራለን እስከ ዘላለም
ሰው በሌለበት ከተማ
ሞት በከበበው ጨለማ
ወገን ገንዘቤ ዘመዴ
በምልጃሽ ቀንቷል መንገዴ
ፋና ሆነሽኝ መብራቴ
በክብርሽ ደምቆልኝ ቤቴ
ሐሴት አረኩኝ ደስታ
ያዘነው ገፄ ተፈታ
አዝ . . . . . . . . .

እንደኔ ሐጥያት በደል
ይገባኝ ነበር መስቀል
ፅኑ ኪዳኗ ጋረደኝ
እምባ ጸሎቷ ታደገኝ
እስኪ ልናገር ስራዋን
የምህረት እናት መሆኗን
ጽዮን እጆቿን ዘርግታ
አስታርቃኛለች ከጌታ
አዝ . . . . . . . . .

የክብር ሰንደቅ አርማዬ
ወደ መቅደሱ መግቢያዬ
አንቺን ይዣለሁ ጠበቃ
የሞቴ ታሪክ አበቃ
እልል እላለሁ ከልቤ
ለቅሶዬ ሰምሮ ሐሳቤ
ድንግል ፍቅር ናት ሰላም
ለክብሯ ይስገድ አለም
አዝ . . . . . . . . .

የእልፍኜ ማማር ውበቴ
ትሩፋቴ ነሽ ሙላቴ
ስምሽ መቀነት ሆኖኛል
የዛለው ክንዴ በርትቷል
ባማረው ቤትሽ አድጌ
በልጅሽ ጸጋ በልፅጌ
በእናትነትሽ በረከት
ይኸው ቆሜያለሁ በህይወት
አዝ . . . . . . . . . /2x/

††† ††† †††
 

Download it here

እረኛዬ ነህ


እረኛዬ ነህ /2x/ የነብሴ ቤዛዋ
የቆሰልክላት አንተ የሞትክላት ባለውለታዋ
ልሰማራ ልውጣ እንጂ ተማምኜ
አንተ ካለህ ታዳጊ እና አዳኜ
የአለም ሰልፏ ብዙ ነው በፍራቻ
የኔ ሞገስ አጀቤ አንተ ብቻ

አዝ . . . . . . . . .
በቁጣህ ቀን ቤቴ በእሳት ሲታጠር
አንተ ባትኖር እኔም የለሁም ነበር
የማያልፈው አለፈ በህይወቴ
ጋርደህልኝ ከልለኸኝ አባቴ

አዝ . . . . . . . . .
እንዳልደክም እንዳልሞት በመንፈሴ
ከቶ አትስጠኝ አሳልፈህ ለራሴ
ከፍ ያልክ ነህ ከፍ ያልከው በምስጋና
ሁሌም አዲስ ጉልበት የምታጸና

አዝ . . . . . . . . .
ጎደለልኝ የመከራው ሙላቱ
በአንተ ታዞ በጊዜው በሰአቱ
የሳኦል ጦር አለፈ በራሴ ላይ
እንደዘበት ከሞት ጋር ሳልገናኝ
አዝ . . . . . . . . . /2x/
††† ††† †††
 

Download it here

እንደ እግዚአብሔር ያለ


እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለምና /2x/
እልል በሉ ቁሙ ለምስጋና /2x/
ባህር ተከፈለ እስኪታይ መሬቱ
ፈርኦን ወደቀ አልሰራም ትምክህቱ
ደካሞቹም ፀንተው ተራመዱ
ሐይለኞቹም ይኸው ተዋረዱ

አዝ . . . . . . . . .
የኢያሪኮ ቅጥር የማይደፈረው
ይኸው ፈራረሰ የሰው እጅ ሳይነካው
ሐይለኞቹም ቢበረታቱብን
እንፀናለን በእርሱ ተደግፈን

አዝ . . . . . . . . .
የተወረወረው የጠላታችን ጦር
ሜዳ ላይ ወደቀ ጋሻ ሆኖ እግዚአብሔር
ለስላሴ ይድረስ ምስጋናችን
ተሸነፈ አዳኝ ጠላታችን

አዝ . . . . . . . . .
ባህር ላይ ሲራመድ ሞገስ አለው እርሱ
በግርማ ሲነሳ ሰጥ ይላል ነፋሱ
የድንግል ልጅ እኛ የምናመልከው
ከሃሊ ነው የለም የሚመስለው

አዝ . . . . . . . . . /2x/
††† ††† †††
 

Download it here

እንዳንተ ያለ እረኛ


ፍቅር ነህ አባቴ ፍቅር ነህ ፍቅር ነህ ጌታዬ
በሰላም እኖራለሁ አልፎልኝ ያ ሁሉ ስቃዬ
ከቁጥር በዝቶ ሃጥያቴ በደሌ ቢያስጨንቀኝም
ተስፋ ቆርጬ በራሴ ለማረፍ ሞቴን በመኝም
አልተሟጠጠም ትእግስትህ ለልጅህ ያለህ ፍቅር
አልነቀልከኝም ጨክነህ ህይወቴ ስልህ ልኑር

አዝ . . . . . . . . . . . . . . . . . .
እንዳንተ ያለ እረኛ እንዳንተ ያለ ወዳጅ
የትም አላገኝ ስፈልግ እድሜ ዘመኔን ብፈጅ
ፍቅር ነህ አባቴ ፍቅር ነህ ፍቅር ነህ ጌታዬ
በሰላም እኖራለሁ አልፎልኝ ያ ሁሉ ስቃዬ

አዝ . . . . . . . . . . . . . . . . . .
ገድቡን አልፎ ሃዘኔ ሲሰብረው ጽኑ ልቤን
ብቻዬን መሆን ፈለግኩኝ መሸከም ከብዶኝ ስድቤን
እያቃሰትኩኝ ፈለኩህ እየታመምኩኝ አባቴ
አስተውያለሁ ፍቅርህን ተስለህብኝ ከፊቴ

አዝ . . . . . . . . . . . . . . . . . .
ምርጫዬ ስህተት አይደለም ማፍቀሬ አንተን ለይቼ
እመሰክራለሁ ስላንተ ሳላፍር አፌን ሞልቼ
ምክንያት አትሻም ስትወደኝ ባዶ ሆኜ ነው ያየኸኝ
ከሸለቆ ውስጥ ተጥዬ ለዛሬው ክብር ያሰብከኝ

አዝ . . . . . . . . . . . . . . . . . . /2x/
††† ††† †††
 

Download it here

እግዚአብሄር ስራው ድንቅ ነው


እግዚአብሄር ስራው ድንቅ ነው
ለኔ ያደረገው ብዙ ነው
እረዳቴ እርሱ ነው ከሰማያት
እግዚአብሄር ጠባቂ ለኔ ህይወት
ብርሃኑን በፊቴ የሚያበራ
አምላኬ ድንቅ ነው የእርሱ ስራ

አዝ . . . . . . . . . . . .
በመንገዴ ሁሉ የሚመራኝ
ስነሳ ስወድቅም የሚያስበኝ
ማንም አልመጣልኝ ከወገኔ
ከሁሉም ይበልጣል እርሱ ለእኔ

አዝ . . . . . . . . . . . .
የእዳዬን ደብዳቤ ውድቅ አድርጎ
ህይወቴን መራልኝ ወደ በጎ
ኧረ እንደ እግዚአብሄር ማን ይሆናል
እርሱን ለሚፈሩት ይታመናል

አዝ . . . . . . . . . . . .
አንድ ቀን አስቤ ተጨንቄ
ለመኖር አልቻልኩም ተጠንቅቄ
ሁሉን ነገር ለእርሱ ትቼዋለሁ
በምህረቱ ጥላ እኖራለሁ

አዝ . . . . . . . . . . . . /2x/ ††† ††† †††
 

Download it here

ዕፁብ ድንቅ ነው ውለታው


ዕፁብ ድንቅ ነው ውለታው
እግዚአብሔር ለኛ ያረገው
ከቶ አይጥለንም ለዘላለም
እንደ አምላካችን ማንም የለም
ወድቀን ነበረ ተነስተናል
ባህር አቁሞ አሻግሮናል
ድንቅ አደረገ ተአምር ሰራ
እያንሳፈፈ ያን ተራራ

አዝ . . . . . . . . .
የጠፋዉን በግ የፈለገ
እራሱን ባዶ ያደረገ
መስቀል ታቅፎ ክንዱ ዛለ
ምን ያልሆነልን ነገር አለ

አዝ . . . . . . . . .
ከአባትም በላይ አባት ነው
የልጆቹ እንባ የሚገደው
የጭንቀታችን ተካፉይ
አዛኝ ጌታ ነው ሁሉን ቻይ

አዝ . . . . . . . . .
ዳግም እንድንቆም በህይወት
ፍጹም ወደደን እስከሞት
ከእንግዲህ አንፈራም እንፀናለን
ለክፉ የማይሰጥ አባት አለን
አዝ . . . . . . . . . (2x)
††† ††† †††
 

Download it here

ወደ ማደሪያው ገብቼ


ወደ ማደሪያው ገብቼ ልስገድ ለእግዚአብሔር
ምስጋናንም ላቅርብ ስለ ስሙ ክብር /2x/
አድርጎልኛልና አመሰግነዋለሁ
በአፀደ መቅደሱ እሰግድለታለሁ
ከፊቱ ለመቆም ማልጄ እነሣለሁ /2x/

አዝ . . . . . . . . . . . . . . . . . .
በመከራዬ ቀን ሆኖኛል መከታ
ቤቱ ተገኝቼ በፍጹም ደስታ
የከንፈሬን ፍሬ ልሰዋ በዕልልታ /2x/

አዝ . . . . . . . . . . . . . . . . . .
ዐሥር አውታር ባለው በበገና
በመላእክቱ ፊት ለማቅረብ ምስጋና
የአፌንም ነገር ሰምተኸኛልና/2x/

አዝ . . . . . . . . . . . . . . . . . .
ለስሙ ልንበርከክ ለእርሱ እንደሚገባ
ስእለቴን ልፈጽም ላቅርብለት መባ
ወደ አደባባዩ በምስጋና ልግባ /2x/

አዝ . . . . . . . . . . . . . . . . . .
አሸበሽባለሁ ድምፄን አሰምቼ
በቤተ መቅደሱ ሌሊት ተገኝቼ
እንደ ካህናቱ እጆቼን ዘርግቼ /2x/

አዝ . . . . . . . . . . . . . . . /2x/
††† ††† †††
 

Download it here

ዝም አትበሉ እግዚአብሔርን አመስግኑ


ዝም አትበሉ እግዚአብሔርን አመስግኑ(2x)
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ በሉ
መላእክትን ሁኑ ምስጋናን ጨምሩ ቅዱስ ቅዱስ በሉ
የሙሴ እህት ማርያም ከበሮውን አንሺው
በምስጋና መዝሙር እግዚአብሔርን ጥሪዉ
አምላክን እናክብር እንዘምር በእልልታ
ከኛ ጋር ይሆናል የሠራዊት ጌታ (2x)

አዝ . . . . . . . . . . . .
ፍጥረታትም ጩሁ ሰማያት ዘምሩ
ስለቅድስናዉ ዉዳሴ ጀምሩ
ዳዊት ሆይ ተነሣ ስለጽዮን ዘምር
ከበሮ ይመታ በገና ይደርደር (2x)

አዝ . . . . . . . . . . . .
ወገኖች እንዘምር ለእግዚአብሄር ክብር
ውለታው ብዙ ነው ለኛ ያለው ፍቅር
ማዳኑን ያያችሁ ዘምሩ በእልልታ
ለጌታ ለእግዚአብሄር ለሰራዊት ጌታ (2x)

አዝ . . . . . . . . . . . .
ባህሩን አቋርጦ ወንዝ ያሻገራችሁ
ተራራውን ንዶ ያገለለላችሁ
በአውሎ ንፋስ መሃል መንገድ አለው ጌታ
ለንጉስ ክርስቶስ እንዘምር በእልልታ (2x)

አዝ . . . . . . . . . . . . /2x/
††† ††† †††
 

Download it here

የሚመስልህ የለም


የሚመስልህ የለም የኛ መድሐኒአለም (2X)
ከፍ በል በአለም እሰከ ዘለዓለም (2X)
ሰማይና ምድርን በቃልህ አጽንተሃል
እልፍ አእላፋትን መላእክትን ፈጥረሃል
በአፍህ እስትንፋስ ሰውን አኑረሃል
የኛ መድሐኒአለም ምን ይከፈልሃል (2X)

አዝ . . . . . . . . . . . . . . .
የኛን ሰጋ ለብሰህ በምድር ታይተሃል
ጎባጣን አቅንተህ እውር አብርተሃል
ሽባውን ተርትረህ ዲዳን አናግረሃል
የሚሳንህ የለም ሁሉም ይቻልሃል (2X)

አዝ . . . . . . . . . . . . . . .
በነፍስም በስጋም ሰውን ፈውሰሃል
ኅብስቱንም ባርከህ ሁሉን አጥግበሃል
የሰይጣንን ሴራ ኃይሉን አክሽፈሃል
በጨለማ ላሉ ብርሃን ሆነሃል (2X)

አዝ . . . . . . . . . . . . . . .
በመስቀል ላይ ሆነህ ሞትንም ሽረሃል
ለሰው ልጆች ሁሉ ትንሳኤን ሰጥተሃል
ወደ ቀድሞ ክብርህ ከፍ ከፍ ብለሃል
በአባትህ ቀኝ ዛሬም ይኸው ተቀምጠሃል
የኛ መድሐኒአለም ክብር ይገባሃል (2X)

አዝ . . . . . . . . . . . . . . . /2x/
††† ††† †††
 

Download it here

የፍቅር እናት የሰላም


የፍቅር እናት የሰላም /2/
ይናፍቀኛል ስምሽን ሳልጠራው ስቀር ማርያም
በህይወቴ ውስጥ በኑሮዬ
ቅደሚ ክፊት ከኋላዬ
ተደላደለ ልቤ
አንቺ አለሽና ካጠገቤ
አዝማች. . . . . . . . .

ምኞቴም ይስመር ድብቅ ህልሜ
ልለፍ ወጀቡን ተቋቁሜ
የጌታዬ እናት ነሽ
ሀይልን ያደርጋል ጸሎትሽ

አዝማች. . . . . . . . .
እንዴት እቀራለሁ ከመንገድ
አደራ እናቴ አስቢኝ
ለሚያስጨንቀኝ ጠላት
ለሚያሳድደኝ አጽጪኝ
አዝማች. . . . . . . . .
ትላንትም ዛሬም አመስጋኝ ነኝ
የለም ለነገ የሚያስፈራኝ
ሜዳ ይሆናል ተራራ
አንቺ አለሽና ከኔ ጋራ
አዝማች. . . . . . . . . /2x/

††† ††† †††
 

Download it here

ደስ ይበልሽ


ደስ ይበልሽ ደስ ይበልሽ
ማርያም ንጽህት ድንግል ደስ ይበልሽ
ከሴቶቹ ሁሉ የተባረክሽ ነሽ
ሰላም እልሻለሁ ማርያም ድንግል
እንደ ብስራታዊው ገብርኤል
ላንቺ የተሰጠሽ ሁለት ድንግልና
አንደኛው በስጋ ሌላው በህሊና

አዝ . . . . . . . . . . . . . . .
ከአለም ሁሉ ሴቶች ንጽህት በመሆንሽ
ሰማያዊው ምስጢር የተገለጸልሽ
የልኡል ማደሪያ ለመሆን የበቃሽ
የጌታችን እናት ድንግል ደስ ይበልሽ

አዝ . . . . . . . . . . . . . . .
የተነበየላት ህዝቅኤል ነብይ
የተዘጋችው በር ብሎ በራእይ
ሳይከፍት ገብቶ ወጣ የእስራኤል ጌታ
ደግሞም ለዘላለም ኖራለች ተዘግታ
አዝ . . . . . . . . . . . . . . .
ማርያም ስትጎበኛት ወደ ቤቷ ገብታ
ኤልሳቤት ዘመረች በመንፈስ ተሞልታ
በማህጸኗ ያለው ዘለለ በደስታ
እኛንም ትጎብኘን ከጥዋት እስከ ማታ
አዝ . . . . . . . . . . . . . . . /2x/
††† ††† †††
 

Download it here

ገብርኤል ሀያል


ገብርኤል ሀያል መልአከ ሠላም መልአከ ብሥራት
የምታወጣ የእግዚአብሄርን ሕዝብ ከሚነድ እሳት
ፍቅርህ ተስሏል በልባችን ፊጥ ቆመናል ባረከን በለን
የጽናታቸው ዝናው ሲሰማ
ከዚያች ባቢሎን ከሞት ከተማ
ሕጻናት ሳሉ በራ እምነታቸው
ቆመህ ተገኘህ መሃከላቸው

አዝ . . . . . . . . . . . .
ውሃው ሲዘልል ቢያስደነግጥም
በጋኖቹም ውስጥ ቢነዋወጥም
ጸንተው ዘመሩ ልጅና እናቱ
አንተ ስትደርስ ከዚያ ከእሳቱ

አዝ . . . . . . . . . . . .
ቂርቆስም ጸና ሞትን ሳይፈራ
አንተ ስላለህ ከእነርሱ ጋራ
አትፍሪ አላት ስለምን ትፍራ
አምነው ድል ነሱት ያንን መከራ

አዝ . . . . . . . . . . . .
እኔም አምናለሁ አድነኝ ብዬ
ቆመህ አማልደኝ ከቸር ጌታዬ
ክፉውን ዘመን የማልፍበትን
ጽናትን ስጠኝ ድል ልንሳበት
አዝ . . . . . . . . . . . ./2x/
††† ††† †††
 

Download it here

ገብርኤል በሰማይ


ገብርኤል በሰማይ ኤልሳቤጥ በምድር
ይመሰክራሉ ድንግል ያንችን ክብር
ትፀንሲ ሲልሽ በከበረ ዜና
ይሁንልኝ አልሽው ትውልድ እንዲፅናና
ከገብርኤል ሰምተው መላእክቱ ሁሉ
ለበጉ ማደሪያ ክብርን ይሰጣሉ
ብፅእት እንላለን እኛም አደግድገን
የራማውን መልአክ አብነት አድርገን

አዝማች . . . . . . . . . . . . . . .
ስራሽ በምድር ነው ሐረግሽ ከሰማይ
ንፁህ መሶበ ወርቅ የተሞላሽ ሲሳይ
የማህፀንሽ ፍሬን በላነው ጠጣነው
በኤፍራታ ሰምተን በዱር አግኝተነው
የተሰወረውን መና በልተነዋል
ከተመረጡት ጋር ብፅእት ብለናል

አዝማች . . . . . . . . . . . . . . .
ከተፈጥሮ በላይ ጽንስን ያዘለለ
የእሳት ምሶሶ ባንቺ ተተከለ
የእግዚአብሄር ሃገሩ የእንጀራ ቤታችን
ምንኛ ድንቅ ነው ክብርሽ እናታችን
ብፅእት እንላለን እኛም አደግድገን
ቅድስት ኤልሳቤጥን አብነት አድርገን

አዝማች . . . . . . . . . . . . . . .
ተወልዶ በግርግም ተኝቶ ስላዩት
ስውና መላእክት አብረው አከበሩት
የጥሉ ግድግዳ በልጅሽ ፈረሰ
በዳግሚት ሔዋን የአዳም ዘር ተካሰ
እጅ እንነሳለን ሆነን በትህትና
ክብርሽን መመስከር ክብራችን ነውና

አዝማች . . . . . . . . . . . . . . .
ተወልዶ በግርግም ተኝቶ ስላዩት
ሰውና መላእክት አብረው አከበሩት
የጥሉ ግድግዳ በልጅሽ ፈረሰ
በዳግሚት ሔዋን የአዳም ዘር ተካሰ
ብፅእት እንላለን እኛም አደግድገን
የራማውን መልአክ አብነት አድርገን
አዝማች . . . . . . . . . . . . . . . /2x/
††† ††† †††
 

Download it here

አይሰለቸኝም ከቶ


አይሰለቸኝም ከቶ ውዳሴ መዝሙር ቅኔ
ብዙ ነው ያረገልኝ እግዚአብሔር በዘመኔ
ቸርነቱና ፍቅሩን ያላራቀ ከባርያው
በለመለመ ስፍራ በጎቹን የሚያሰማራው
ልዩ ነው የኛ ንጉስ ልዩ ነው የኛ ጌታ
መጽሐፉን የገለጠ ማህተሙን የፈታ

አዝ . . . . . . . . . . . .
አንገቱን ፍጹም ደፍቶ ቀና እንድል አድርጎኛል
እየታመመ ሞቶ በህይወት አቁሞኛል
አልችልም የሱን ፍቅር መዘርዘርና ማውራት
ውልታውን ለመግለጽ የለኝም ብርቱ ቃላት

አዝ . . . . . . . . . . . .
ያንተ ክንድ የማይችለው ተራራ ጋራ የለም
ወጥቻለሁ ከጥልቁ ታላቅ ነህ ለዘላለም
የተከፈተ ደጃፍ ሰጥተኸኛል በፊቴ
ተመስገን ክበርልኝ ንገስልኝ አባቴ

አዝ . . . . . . . . . . . .
ለይተህ የጠራኸኝ ያበዛህልኝ ጸጋ
ትዝታዬ ነህ ጌታ ሲመሽና ሲነጋ
ወዳጅና ዘመዴ ብዬ ስጠራህ ልኑር
ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ ለወጠኝ ያንተ ፍቅር

አዝ . . . . . . . . . . . . /2x/
††† ††† †††
 

Download it here